EthioPoint: Ethiopians Analysis | Research Articles

እንደ ዳይኖሰር እየጠፉ የሚገኙ ተቋማት ትኩረት ይሰጣቸዉ።

8 mins read

ጎንደር
ልሁል አለም
በአማራ ክልል ዉስጥ በተለይም በጎንደር የሚገኙ እረዘም ላለ አመታት ከስራ ዘርፋቸዉ የተቋረጡ ተቋማት ወደ ጥቅም ላይ ይዉሉ ዘንድ እየተጠየቀ ይገኛል።
ተቋማቶቹ በስራ ላይ ቢዉሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ስራ አጦችን ወደ ስራ ዘርፍ ከማካተታቸዉ በተጨማሪ ለመንግስትም መሰረታዊ የገቢ ምንጭ በመሆን ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖራቸዉ የሚታወቅ ነዉ።
ተቋማቱ አግባብ ባልሆነና ምክንያታቸዉ በዉል በማይታወቅ መልኩ እረዘም ላለ አመታት ትኩረት የተነፈጋቸዉ በመሆናቸዉ ወደ ልማት ሊመለሱ ይገባል።
ከእነዚህ ተቋማቶች መካከል በጥቂቱ…
1.ፎገራ ሆቴል _ አገልግሎት መስጠት ካቆመ እረጅም ወቅት የሚያስቆጥር ሆኖ ሳለ በአሁኑ ወቅት ምን እየተከናወነብት እንደሆነ እንኳን በዉል የማይታወቅ ነዉ፡፡
39071421 220767971926885 9098367524805804032 n
2. ተራራ ሆቴል _ ይህ ሆቴል ከመሰረታዊ የልማት ተቋምነቱ እንዲቋረጥ ከተደረገ ወዲህ በቀጥታ በበላይነት እና ያለአግባብ የአጋዚ ጦር ካምፕ እንዲሆን ተደርጓል ይህ አግባብነት የሌለዉ ተግባር ባስቸኳይ ቆሞ ፎገራ ሆቴል ለህዝብና ለሐገር የሚገባዉን ጥቅም እንዲያገኝ ተደረጎ የአጋዚ ጦር ከሰፈረበት ሆቴል ወደ ካምፕ እንዲሸጋገር ለመጠየቅ እንወዳለን።
3. ጎንደር ማተሚያ ቤት _ የጎንደር በቂ የሆነ የማተሚያ ቤት አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል አንዳንድ ግዜ ከዉድድርና ከዋጋ አንጻር የተለያዩ ህትመቶችን ለማከናወን እስከ አዲስ አበባ ድረስ መሄዽ ግዴታ ነዉ ጎንደር ጸሀፊያን ከይያኒያን አሏት ሁሉም በግዘ ደረጃዉ የሚያድግ ስራቸዉን ለማሳተም ተወዳዳሪ ተቋም በከተማቸዉ ዉስጥ ያስፈልጋቸዋል ይህ ማለት ማተሚያ ቤት የለም ለማለት ተፈልጎ አይደለም ነገር ግን ያለንን ማተሚያ ቤት ድርግም አድርጎ ዘግቶ አቅም ማመናመን ወንጀል ነዉ አንድ ተቋም ሲዘጋ ምክንያቱን ህዝብ ማወቅ አለበት እንዲከፈት ህዝብ ጥረት እንዲያደርግ መንግስት ሐላፊነቱን ይወጣ የተዘጉ ተቋማትን ፈትሾ ወደ ስራ ይመልስ።
39121819 748498155543106 5015336395049271296 n 1
4. ኢዲዲሲ(ጅንአድ) _ ይህ ተቋም በብዙ የሀገራችን ክፍሎች የት እንደደረሰ እንኳን የማይታወቅ እንደ ዳይኖሰር የጠፋ ተቋም ነዉ በጎንደር የሚገኘዉ ይህ መስሪያ ቤት ተዘግቷል ከመዘጋቱ በተጨማሪ ድርጅቱ ወደ ተለዋጭ ልማት አልገባም ለምን የሚለዉን መጠይቅ የሚመለከተዉ አካል አፋጣኝ ምላሽ እንደሚሰጥበት ይጠበቃል።